እንኳን ደህና መጡ!

በባህሩ ዳርቻ ሮዝ ቦት ጫማዎች የለበሰች ትንሽ ልጅ አሸዋ ላይ በባልዲ እና በውሃ እየተጫወተች።

አንድ ሴት በመንገድ ላይ በአረንጓዴ የቆሻሻ መጣያ ቆርቆሮ ውስጥ ቢጫ ኩባያ ስታስቀምጥ።

ምን እየሆነ ነው?

null

የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች ስልታዊ የንግድ ሥራ እቅዳችንን እያዘመነ ነው። ይህ እቅድ ለደንበኞቻችን እና ማህበረሰቦቻችን የምንሰራው ሥራ የገንዘብ ቁርጠኝነታችን ላይ እንድንስራ እና ማስተዳደር ላይ እንድናተኩር ይረዳናል። ይህ ዝመና የሚከተሉትን ያደርጋል:

 • ስራችንን እንዴት እንደምንመርጥ/ እንደምንሰራ የደንበኛ እና የማህበረሰብ ግብረ መልስን ያንጸባርቃል
 • ጎልቶ የሚታየውን ተነሳሽነት እና መዋዕለ ንዋዮች ላይ ይገነባል
 • በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ውስጥ ስለ ፍጆታ መገልገያዎች የሂሳብ ለውጦች ግልፅነት ይሰጣል
 • የአፈጻጸም መለኪያዎችን ያድሳል

በ2024 የተሻሻለውን እቅድ ለሲያትል ከተማ ከንቲባ እና ለከተማ ምክር ቤት እንዲያጸድቁት እናስገባለን።

ስልታዊ የንግድ እቅድ ማሻሻያ መርሃ ግብር

ነሐሴ 2023–
ጥቅምት 2023

የማህበረሰብ ግብረ መልስ ተሳትፎ እና ስብሰባ ማድረግ

ህዳር 2023–
የካቲት 2024

የተዘመነውን እቅድ ማዳበር

መጋቢት 2024–
ሰኔ 2024

እቅዱን መቀበል/ ማጽደቅ እና ማተም

”>የሲያትል

የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች (SPU) ምንድን ነው?

SPU በየቀኑ ጤናማ፣ የበለጸጉ ማህበረሰቦችን ለማረጋገጥ የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች በየእለቱ፣ የህዝብ ጤናን እና የአካባቢ አየር ንብረታችንን በመጠበቅ አስፈላጊ፣ ህይወትን የሚጠብቁ አገልግሎቶችን ያቀርባል። ሲያትል የህዝብ መገልገያዎች (SPU) ለቀጣይ ትውልዶች ሲባል የአካባቢ አየር ንብረታችንን ለመጠበቅ ፍትሃዊ የውሃ አያያዝ እና የቆሻሻ ሃብቶች አስተዳደርን ለማድረግ ቁርጠኛ ነው።

ስለ ሲያትል የህዝብ መገልገያዎች (SPU) የበለጠ ለማወቅ ይፈልጋሉ? የእኛን ድረ-ገጽ ይፈትሹ

የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች ተልእኮ: የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች ከማህበረሰባችን ጋር በሽርክና አብሮ በመሥራት ለዛሬ እና ለወደፊት ትውልዶች ሲባል የውሃ እና የቆሻሻ ሀብቶችን በፍትሃዊነት በማስተዳደር ጤናማ ሰዎች፣ የአካባቢ አየር ንብረቶች፣ እና ኢኮኖሚ እንዲኖር ያበረታታል።

የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች አስፈላጊ አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው?

የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች አስፈላጊ አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው?

በሲያትል ውስጥ ላሉ ነዋሪዎች እና ንግዶች የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃ፣ የዉሃ ፍሳሽ ማስወገጃ፣ የመጠጥ ውሃ፣ እና የቆሻሻ ማሰባሰብያ አገልግሎቶችን እናስተዳድራለን እንዲሁም እንዲቆዩ እንይዛለን። የእኛ የንድፍ፣ የጥገና፣ እና የግንባታ እንቅስቃሴዎች ለነዋሪዎች፣ ለንግዶች እና ጎብኝዎች አስተማማኝ አገልግሎት መስጠት እንደምንችል ያረጋግጣሉ።

 • የመጠጥ ውሃ: ከብክልና የተጠበቁ የተራራ የውሃ ተፋሰሶች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ
 • የዉሃ ፍሳሽ ማስወገጃ እና የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃ: ጤናዎን የሚጠብቁ እና ክምችቶችን፣ ጎርፍን፣ እና ብክለትን፣ የሚቀንሱ የፍሳሽ እና የቆሻሻ ፍሳሽ አገልግሎቶች
 • ቆሻሻ/እንደገና ጥቅም ላይ የሚዉሉ/ኮምፖስት ፡ የቆሻሻ አሰባሰብ፣ አወጋገድ፣ እና ቅነሳ ፕሮግራሞች
 • ንፁህ ከተማ፡የሲያትልን ንፅህና እና ደህንነት ለመጠበቅ ቆሻሻዎችን፣ ግራፊቲዎችን፣ መርፌዎችን፣ ህገወጥ ቆሻሻ መጣልን እና ሌሎች አደገኛ ነገሮችን ማስወገድ።

በየአመቱ የሚከተሉትን ስራዎች እንሰራለን፥

 • 40+ ቢሊዮን ጋሎን የመጠጥ ውሃ ማቅረብ
 • 1,200+ ማይሎች የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች እና 1,000+ ማይሎች የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓዶችን እና ቧንቧዎችን መጠገን
 • 22+ ሚሊዮን የቤት ውስጥ ቆሻሻዎችን፣ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን፣ እና ኮምፖስትን በመሰብሰብ ማስተባበር
 • 5+ ሚሊዮን ፓውንድ ቆሻሻን ከህዝብ ቦታዎች ማስወገድ
 • ከእርስዎ እና ከማህበረሰባችን ጋር ለመሳተፍ ከ 50 በላይ የደንበኛ ፕሮግራሞችን ማቅረብ
 • እና ከዚህም በላይ በጣም ብዙ!
ስልታዊ የንግድ እቅድ ምንድን ነው?

ስልታዊ የንግድ እቅድ ምንድን ነው?

ስልታዊ የንግድ ሥራ እቅዱ የአገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቱ የውሃ እና ቆሻሻ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ መዋዕለ ንዋዮች፣ እና በፍጆታ ዋጋ ላይ የተደረጉ ለውጦችን ይዘረዝራል። የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች ከማህበረሰቡ ጋር በሽርክና እንዴት እንደሚሰሩ የሚያሳይ መመሪያ ነው፤ ማደራጀት፣ ኢንቨስት ማድረግ፣ እና እራሳችንን መገምገም፣ እና እራሳችንን ለፍትሃዊ እኩልነት፣ ለተመጣጣኝ ዋጋ፣ እና የአካባቢ አየር ንብረት ጥበቃ ስራ እናውላለን።

ስልታዊ የንግድ ሥራ እቅዱ አራት የትኩረት አቅጣጫዎች አሉት:

 • አስፈላጊ አገልግሎቶችን ማቅረብ። ደህንነቱ የተጠበቀ የቧንቧ ውሃ ማቅረብ፣ ብክነትን እና ቆሻሻን መቀነስ፣ የቆሻሻ ውሃ እና የዝናብ ውሃን ማስተዳደር እና ለደንበኞች ምላሽ መስጠት።
 • አካባቢን እና ጤናን መጠበቅ። የውሃ ምንጮችን መጠበቅ፣ በውሃ አስተዳደር እና ስርዓት ላይ የተቀናጀ እና ፍትሃዊ መዋዕለ ንዋዮችን ማሳደግ፣ እና የሲያትልን ብክነትን እና የካርቦን ብክለትን በመቀነስ ኢኮኖሚያችንን ማሳደግ።
 • ደንበኞቻችንን፣ ማህበረሰቡን፣ እና ሰራተኞቻችንን ማበረታታት። የፍጆታ አገልግሎቶችን ተደራሽነትን ማሻሻል፣ አብሮ መኖር መቻልን እና የአካባቢ እድል እንዲጨምር ከማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ሽርክና ማድረግ። የበለጠ የተለያዩ ገጽታ እና ተለዋዋጭ የሰራተኛ ኃይል ማዳበር እና ማስተዋወቅ።
 • የንግድ ልምዶችን ማጠናከር። አገልግሎቶችን ለማቅረብ እና የንብረት ምንጮችን እና አደጋዎችን በመቆጣጠር ረገድ መላመድ እና ፈጠራዎችን በመጠቀም የህዝብ መገልገያዎች የደንበኛን ተመጣጣኝ ዋጋ አቅም ማሻሻል።

የበለጠ ለማወቅ የአሁኑን 2021–2026 ስልታዊ የንግድ ሥራ እቅድን ይመልከቱ።

ለምንድነው ስልታዊ የንግድ ሥራ እቅዳችን ማሻሻያ የሚያስፈልገው?

ለምንድነው ስልታዊ የንግድ ሥራ እቅዳችን ማሻሻያ የሚያስፈልገው?

ትኩረታችን ከምናገለግለው ማህበረሰብ ወቅታዊ ፍላጎቶች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ለደንበኞቻችን በፍጆታ ዋጋዎች ላይ የሚገመቱ እና የመረጋጋት ለውጦችን ለማቅረብ ይህንን እቅድ በየሦስት ዓመቱ እናዘምነዋለን። የሚቀጥለው ዝመና በ2024 ላይ ነው፣ እና እርስዎ የህዝብ መገልገያ የወደፊት ሁኔታን እንዲቀርጹ እንዲያግዙ እንፈልጋለን።